Thursday, June 7, 2018

Feature story





በ ፎዚያ  ሱነሞ       የጀምበርን ማዘቅዘቅ ተከትሎ በሀገራችን አውራ ጎዳናዎች ላይ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ አልያም በጓደኝነት ህብረት የሚራመዱ ወይም  የሚያደርጉ ሰዎችን ማየት የተለመደ ተግባር ሆኖዋል፡፡
ነገር ግን አብዛኞቻችን ወክ የምናደርገው እንዲው ስለለመድነው እንጂ የሚያስገኘውን ጥቅም ተገንዝበን አደለም፡፡ የተለያዩ ጥናቶች ወክ ማድረግ ብዙ ትሩፋቶችን እንደሚያስገኙ ያመለክታሉ፡፡ ከዚ በመነሳት ወክ ማድረግ  ምን  እሚያስገኘው  ጥቅም አለ ስንል ጠይቀን ነበር፡፡ የጥያቅያችን  መልሶች የሚከተሉት  ናቸው፡፡
መግብያ 
እኔ ወክ የማደርገው  እንዲሁ ደስ ስለሚለኝ  ነው እንጂ ጥቅሙን ተረድቼ አይደለም፡፡  መውጫ
መግብያ
ከጓዶኞቼ  ጋር  ወክ ማድረግ  በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ምክንያቱም  ቀን ሙሉ ውለን ማታ ተገናኝተን  ወክ  ስለምናደርግ  በጣም ይናፍቀኛል፡፡ የሚሰጠኝ ደስታ  ልዩ  ነው፡፡   መውጫ
መግብያ
እንደምታይኝ  ወፍራም ነኝ፡፡ወክ  በማድረግ  ከተለያዩ  በሽታዎች  ራሴን  እጠብቃለው፡፡ ጤናዬን   ለመጠበቅ ስል  ወክን  አዘወትራለው፡፡   መውጫ
መግብያ
እኔ  ወክ  እማደርገው  ሲከፋኝ፤ብቻዬን  መሆን  ስፈልግ  ነው፡፡ወክ  ብማድርግበት ሰአት  ከራሴ  ጋር  አወራለው፡፡ደግሞ ወክ እማደርገው ብዙ  ግዜ ብቻዬን  ነው፡፡ምክንያቱም  ከራሴ ጋር እንዳወራ ይረዳኛል፡፡ መውጫ
መግብያ
እኔ  ብዙ ግዜ  ወክ  እማደርገው  የማታውን  አየር  ወይም  ቅዝቃዜ  ስለምወደው  ነው፡፡እናም  ምንም  እሚረብሸኝ  ነገር አልፈልግም  በዝምታና  መንገዱ  ላይ  በመመሰጥ  ነው ወክ  እማደርገው፡፡የዛሬዋ  የፍቅር  ጓደኛዬን  ያገኘኋት  እዛው  ወክ  እማዘውትርበት  ስፍራ  ነው፡፡ለኔ  ከሁሉም ጥቅሞች  የበላይ ነው፡፡መውጫ
ምንም  እንኳን  መልካም ጅማሬዎች  ቢኖሩም  አሁንም  የሃገራችን  ከተሞች  ለወክ  አመቺ  የሆኑ  መሰረተ ልማቶች  መዘርጋት  የቤት ስራቸው  ቢሆንም  ባሉት  ምቹ  መሰረተ  ልማቶች  ላይ  ወክን  በማዘውተር  ጤናችንን  እንጠብቅ  ስንል  መልእክታችን  እናስተላልፋለን፡፡


No comments:

Post a Comment

Feature story

The   Increase Number of Illegal Street Vander   affect 6    kilo   Residents Resident   live in gulela sub city worda 3 6 kilo area ...